ብዙ ከሆነው የሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርበው ስብ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የሚቀርበው የመጠጥ ቊርባን ነበር። በዚህ ሁኔታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት እንደገና ተጀመረ፤
ቈላስይስ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሥጋ ከእናንተ ብርቅም እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ በመልካም ሥነ ሥርዓት መኖራችሁንና በክርስቶስ ላይ ያላችሁን ጽኑ እምነት በማየትም ደስ ይለኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም በሥጋ ከእናንተ ርቄ ብገኝ በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ነኝና በሥርዐት መኖራችሁንና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአካል ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፤ መልካሙንም ሥነ ሥርዓታችሁንና በክርስቶስም ላይ ያላችሁን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በሥጋ ከእናንተ ዘንድ ባልኖርም እንኳን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባያችሁንና ሥርዐታችሁን፥ በክርስቶስም ያለ የእምነታችሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል። |
ብዙ ከሆነው የሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርበው ስብ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የሚቀርበው የመጠጥ ቊርባን ነበር። በዚህ ሁኔታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚደረገው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት እንደገና ተጀመረ፤
እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በዐሥራ ሁለት ተከታታይ ቀኖች ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አለቆች አንዱ መሠዊያው ለሚቀደስበት ክብረ በዓል የሚሆን መባ ያቀርቡ ዘንድ ንገራቸው።”
መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን እንኳ አይተውት ስለማያውቁ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ብርቱ ትግል እንደማደርግ ልታውቁ እወዳለሁ።
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ በመለየታችን ስለ እናንተ ያለን ናፍቆት ብዙ ስለ ሆነ በዐይነ ሥጋ ልናያችሁ ብዙ ጥረት አደረግን።