ንግግራቸው ግራ የሚያጋባ፥ ቋንቋቸው ወደማይታወቅና የቃላቸውን ትርጒም ልታስተውለው ወደማትችል ታላላቅ ሕዝቦች ልኬህ ቢሆን ኖሮማ በሰሙህ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 27:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ሲጥሉ የባሕሩ ጥልቀት አርባ ሜትር ያኽል ሆኖ ተገኘ፤ ጥቂት ቈይተው መለኪያውን እንደገና በጣሉ ጊዜ ሠላሳ ሜትር ያኽል ጥልቀት አገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጥልቀት መለኪያውን ገመድ ወደ ታች ጥለው ሲመለከቱት የውሃው ጥልቀት አርባ ሜትር ያህል ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ደግመው ሲጥሉ ጥልቀቱ፣ ሠላሳ ሜትር ያህል ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መለኪያ ገመድም ቢጥሉ ሃያ በሰው ቁመት አገኙ ጥቂትም ቆይተው ሁለተኛ ቢጥሉ ዐሥራ አምስት በሰው ቁመት አገኙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መለኪያ ገመድ ጣሉ፤ በሰው ቁመትም ሃያ አገኙ፤ ከዚያም ጥቂት ፈቀቅ ብለው ዳግመኛ ጣሉ፤ በሰው ቁመትም ዐሥራ አምስት አገኙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መለኪያ ገመድም ቢጥሉ ሀያ በሰው ቁመት አገኙ ጥቂትም ቆይተው ሁለተኛ ቢጥሉ አሥራ አምስት በሰው ቁመት አገኙ፤ |
ንግግራቸው ግራ የሚያጋባ፥ ቋንቋቸው ወደማይታወቅና የቃላቸውን ትርጒም ልታስተውለው ወደማትችል ታላላቅ ሕዝቦች ልኬህ ቢሆን ኖሮማ በሰሙህ ነበር።
በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር መካከል ላይ በነፋስ እየተንገላታን ስንሄድ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞች ወደ ምድር የቀረቡ መሰላቸው።
መርከባችን በባሕሩ ዳር ካሉ ድንጋዮች እንዳይጋጭ ፈርተው ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቆችን ወደ ባሕሩ አወረዱ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ አልፎ ቀን እንዲመጣላቸው ይጸልዩ ጀመር።