እነርሱም ሁሉ ለበዓሉ የሚሆኑትን አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን ለመሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆኑም ዐሥራ ሁለት ፍየሎችን በእያንዳንዱ ነገድ ስም አቀረቡ።
ሐዋርያት ሥራ 26:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚህ ተስፋ ለመድረስ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን እግዚአብሔርን ሌት ተቀን እያመለኩ ይጠባበቁ ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! እኔም በአይሁድ የተከሰስኩበት በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ከልብ እያገለገሉ፣ ሲፈጸም ለማየት የሚተጉለትም ተስፋ ይኸው ነው። ንጉሥ ሆይ፤ አይሁድም የሚከስሱኝ ስለዚሁ ተስፋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደዚህም ወደ ተስፋ ቃል ዐሥራ ሁለቱ ወገኖቻችን ሌሊትና ቀን በትጋት እያመለኩ ይደርሱ ዘንድ አለኝታ አላቸው፤ ስለዚህም አለኝታ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! ከአይሁድ እከሰሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን በመዓልትም በሌሊትም እርሱን እያገለገሉ ወደ እርስዋ ይደርሱ ዘንድ ተስፋ ያደርጋሉ፤ አይሁድም የሚከስሱኝ ስለዚህ ተስፋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚህም ወደ ተስፋ ቃል አሥራ ሁለቱ ወገኖቻችን ሌሊትና ቀን በትጋት እያመለኩ ይደርሱ ዘንድ አለኝታ አላቸው፤ ስለዚህም አለኝታ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ከአይሁድ እከሰሳለሁ። |
እነርሱም ሁሉ ለበዓሉ የሚሆኑትን አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን ለመሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆኑም ዐሥራ ሁለት ፍየሎችን በእያንዳንዱ ነገድ ስም አቀረቡ።
ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጅ በክብር ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት በአዲሱ ዓለም የእኔ ተከታዮች የሆናችሁ፥ እናንተም፥ በዐሥራ ሁለት ዙፋኑ ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።
በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።
አሁንም ያስጠራኋችሁ እንዳያችሁና ይህንንም እንድነግራችሁ ነው፤ እኔ በዚህ በሰንሰለት የታሰርኩት ለእስራኤል በተሰጠው ተስፋ ምክንያት ነው።”
በእርግጥ መበለት የሆነችና ብቻዋን የምትኖር፥ ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋ ሌሊትና ቀን የእግዚአብሔርን ርዳታ በመለመን በጸሎት ጸንታ ትኖራለች።
በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሆነው ከያዕቆብ የተላከ መልእክት፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን።