ሐዋርያት ሥራ 22:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እንዲህ አልኩ፤ ‘ጌታ ሆይ! በየምኲራቡ እየሄድኩ በአንተ ያመኑትን ሁሉ እንዳሰርኩና እንደ ደበደብኩ እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም እንዲህ አልሁት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ በአንተ የሚያምኑትን ሰዎች ለማሰርና ለመደብደብ፣ በየምኵራቡ ስዞር እንደ ነበር እነዚህ ሰዎች ያውቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ‘ጌታ ሆይ! በአንተ የሚያምኑትን በምኵራብ ሁሉ እኔ በወኅኒ አገባና እደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ያውቃሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እንዲህ አልሁት፦ ‘ጌታዬ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በየምኵራቦቻቸው ሳስራቸውና ስደበድባቸው የነበርሁ እኔ እንደ ሆንሁ እነርሱ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በምኵራብ ሁሉ እኔ በወኅኒ አገባና እደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ያውቃሉ፤ |
የክርስትናን እምነት የሚከተሉትን ሁሉ እስከ ሞት የማሳድድ ሰው ነበርኩ፤ ወንዶችንና ሴቶችን እያሰርኩ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አደርግ ነበርኩ።
ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ይጥር ነበር፤ ከቤት ወደ ቤትም እየገባ ወንዶችና ሴቶች አማኞችን እየጐተተ ያወጣ ነበር፤ ወደ እስር ቤትም ያስገባቸው ነበር።