ሐዋርያት ሥራ 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሁሉም ተገርመውና የሚሉትን አጥተው “ይህ ነገር ምን ይሆን!” ተባባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም በአድናቆትና ግራ በመጋባት፣ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ተገረሙ፤ የሚሉትንም አጡ፥ እርስ በርሳቸውም፥ “እንጃ! ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው፦ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ። |
ሄሮድስ በመጀመሪያ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ መሆኑን ስለሚያውቅ ይፈራውና ይጠብቀውም ነበር። ሄሮድስ የዮሐንስን ንግግር በሰማ ቊጥር ይታወክ ነበር፤ ይሁን እንጂ በደስታ ይሰማው ነበር።
ጴጥሮስ የራእዩ ፍች “ምን ይሆን?” እያለ በሐሳቡ ሲጨነቅ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በጥያቄ የስምዖንን ቤት አግኝተው በበር ቆመው ነበር፤