La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 19:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጳውሎስ ወደ ሕዝቡ ለመሄድ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርት ግን እንዳይሄድ ከለከሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጳውሎስም ወጥቶ ሕዝቡ ፊት ለመቅረብ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርት ግን ከለከሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጳውሎስም ወደ ሕዝቡ ይገባ ዘንድ በፈቀደ ጊዜ ደቀ መዛሙርት ከለከሉት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጳው​ሎ​ስም ወደ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሊገባ ወድዶ ነበር፤ ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርት ከለ​ከ​ሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጳውሎስም ወደ ሕዝቡ ይገባ ዘንድ በፈቀደ ጊዜ ደቀ መዛሙርት ከለከሉት።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 19:30
7 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የጸሩያ ልጅ አቢሳ ዳዊትን ለመርዳት መጥቶ በዚያ ኀያል ሰው ላይ አደጋ በመጣል ገደለው፤ ከዚያን በኋላ የዳዊት ተከታዮች ዳግመኛ ከእነርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄድ ዳዊትን ቃል በማስገባት “የእስራኤል መብራት የሆንክ አንተ እንዳትጠፋ ዳግመኛ ወደ ጦርነት አትወጣም” አሉ።


ከእስያ አገር ባለሥልጣኖችም ወዳጆቹ የሆኑ አንዳንዶቹ ወደ ጳውሎስ ሰው ልከው “ወደ ሕዝብ መሰብሰቢያው ቦታ ሄደህ እንዳትታይ” ሲሉ ለመኑት።


አንዳንዶች ግን እልኸኞች በመሆን የጌታን መንገድ በሕዝቡ ፊት እየተሳደቡ አናምንም ባሉ ጊዜ ከእነርሱ ራቀ፤ አማኞችንም ለብቻቸው ወስዶ በጢራኖስ አዳራሽ በየቀኑ ያስተምር ነበር።


ጳውሎስም “እኔ በኪልቅያ በምትገኘውና ዝነኛ በሆነችው በጠርሴስ ከተማ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ እባክህ ለሕዝቡ እንድናገር ፍቀድልኝ” አለው።