እርሱን ትኲር ብዬ ስመለከት በመጋረጃው ጨርቅ ላይ እንስሶችን፥ የዱር አራዊትን፥ በልባቸው የሚሳቡ ፍጥረቶችንና በሰማይ የሚበርሩ ወፎችን አየሁ፤
ሐዋርያት ሥራ 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ጴጥሮስ ሆይ! ተነሥና እያረድክ ብላ!’ የሚለኝንም ድምፅ ሰማሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ፣ ‘ጴጥሮስ ሆይ፤ ተነሣና ዐርደህ ብላ’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ጴጥሮስ ሆይ! ተነሣና አርደህ ብላ፤’ የሚለኝንም ድምፅ ሰማሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሥና አርደህ ብላ’ የሚለኝንም ቃል ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚለኝንም ድምፅ ሰማሁ። |
እርሱን ትኲር ብዬ ስመለከት በመጋረጃው ጨርቅ ላይ እንስሶችን፥ የዱር አራዊትን፥ በልባቸው የሚሳቡ ፍጥረቶችንና በሰማይ የሚበርሩ ወፎችን አየሁ፤