ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
2 ጢሞቴዎስ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን የሚያመልኩ መስለው ይታያሉ፤ የአምልኮትን ኀይል ግን ይክዳሉ፤ እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ራቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሃይማኖትን መልክ የያዙ ነገር ግን ኃይሉን የካዱ ሆነው ይገኛሉ፤ እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ራቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።
በዚህ መልእክት ያስተላለፍንላችሁን ምክር የማይቀበል ሰው ቢኖር እንዲህ ያለውን ሰው ልብ በሉት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አታድርጉ።
ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
በሰውነት ማጠንከሪያ ትምህርት ራስን ማለማመድ ጥቅሙ ጥቂት ነው፤ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለማመድ ግን ለአሁንና ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።
አእምሮአቸው በረከሰና እውነት በጠፋባቸው ሰዎች የሚደረግ የማያቋርጥ ክርክርን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን ማምለክ የሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።
“እግዚአብሔርን እናውቃለን” ይላሉ፤ በሥራቸው ግን ይክዱታል፤ እነርሱ አጸያፊዎች፥ የማይታዘዙና ምንም መልካም ሥራ ማድረግ የማይችሉ ናቸው።