2 ሳሙኤል 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ንጉሥ ዳዊት መፊቦሼትን ከሎደባር ከዓሚኤል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ንጉሥ ዳዊት፣ ሜምፊቦስቴን ከዓሚኤል ከማኪር ቤት ከሎደባር ልኮ አስመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ንጉሥ ዳዊት፥ መፊቦሼትን ከዓሚኤል ከማኪር ቤት ከሎደባር ልኮ አስመጣው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ዳዊት ልኮ ከሎዶባር ከአብያል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ዳዊት ልኮ ከሎዶባር ከዓሚኤል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው። |
የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።