መፊቦሼትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፥ እንደምታውቀው እኔ ሽባ ነኝ፤ ከአንተ ጋር ለመሄድ ፈልጌ አገልጋዬን ‘በቅሎዬን ጫንልኝ’ ብለው ከድቶኝ ሄደ፤
2 ሳሙኤል 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ቸርነት የማሳየው ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ሲል ጺባን ጠየቀው። ጺባም “ከዮናታን ወንዶች ልጆች አንዱ አሁንም በሕይወት አለ፤ እርሱም እግረ ሽባ ነው” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ሲባም ለንጉሡ፣ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም ለንጉሡ፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው አልቀረምን? አለ። ሲባም ንጉሡን፦ እግሩ ሽባ የሆነ አንድ የዮናታን ልጅ አለ አለው። |
መፊቦሼትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፥ እንደምታውቀው እኔ ሽባ ነኝ፤ ከአንተ ጋር ለመሄድ ፈልጌ አገልጋዬን ‘በቅሎዬን ጫንልኝ’ ብለው ከድቶኝ ሄደ፤
ንጉሥ ሆይ! እንዲያውም ስለ እኔ በውሸት ለአንተ የነገረህ ጉዳይ አለ፤ ነገር ግን አንተ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንክ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ።
ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ።
ዳዊትም “አይዞህ አትፍራ! ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ፤ የአያትህ የሳኦል ይዞታ የነበረውን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም በማእዴ ተቀምጠህ ትመገባለህ” አለው።
እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ የነበረው ፍቅር እጅግ ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ፥ ዛሬም አንተን ከብዙ አሕዛብ መካከል መርጦአል፤ አንተም እስከ አሁን የእርሱ ምርጥ ሕዝብ ነህ።