ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤
2 ሳሙኤል 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደማስቆ የሚኖሩ ሶርያውያንም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ለመርዳት ሠራዊት በላኩ ጊዜ ዳዊት አደጋ ጥሎ ኻያ ሁለት ሺህ ጭፍሮችን ገደለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺሕ ሰው ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደማስቆዎቹ ሶርያውያን የጾባን ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎች ገደለ። |
ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤
ከዚያም በኋላ ዳዊት የሶርያ ግዛት የሆነችው የጾባ ንጉሥ የሆነውን የረሖብን ልጅ ሀዳድዔዜርን ድል አደረገ፤ ሀዳድዔዜር ድል በተመታበትም ጊዜ በላይኛው ኤፍራጥስ ወንዝ የሚገኘውን ግዛቱን ለማስመለስ በጒዞ ላይ ነበር።
ግብጻውያን ሰዎች ናቸው እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ ለባሾች እንጂ የተለዩ መናፍስት አይደሉም፤ እግዚአብሔር በቊጣው በሚነሣበት ጊዜ ይህ የሌሎች ረዳት የሆነው መንግሥት ይደናቀፋል፤ እርሱ ይረዳው የነበረውም መንግሥት ተንኰታኲቶ ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድነት ተያይዘው ይጠፋሉ።
ስለምን ቢባል፥ የሶርያ ራስ ደማስቆ ስትሆን፥ የደማስቆም ራስ ረጺን ነው፤ ስለ እስራኤልም የሆነ እንደ ሆነ፥ በስልሳ አምስት ዓመቶች ጊዜ ውስጥ ብትንትናቸው ወጥቶ በመንግሥትነት መታወቃቸው ይቀራል።