La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 7:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ለዘለዓለም ፈጽም፤ ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሆን ዘንድ የተናገርከውን ፈጽም፤ ሰዎችም ልዑል እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው ይላሉ። የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ለባሪያህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአገልጋይህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘለዓለም ጠብቅለት፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ ሁሉን የም​ት​ገዛ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አሁ​ንም ለባ​ሪ​ያ​ህና ለቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ናው፤ አሁ​ንም እንደ ተና​ገ​ርህ አድ​ርግ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤቱ አምላክ ሆይ፥ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የተናገርኸውን ለዘላለም አጽናው፥ እንደ ተናገርህም አድርግ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 7:25
11 Referencias Cruzadas  

‘መልካም ነገር አደርጋለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛልሃለሁ’ ያልከውን አስታውስ።”


እስራኤልንም ለዘለዓለም ሕዝብህ አደረግህ፤ ጌታ ሆይ፥ አንተም አምላካቸው ሆንክ።


በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።


አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ! አገልጋይህ ለነበረው ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግ።


እንግዲህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋይህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግልኝ።


ለእኔ ለአገልጋይህና ለሚፈሩህ ሁሉ የሰጠኸውን የተስፋ ቃል ፈጽም።


ተስፋ የማደርገው በእርሱ ላይ ስለ ሆነ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኸውን የተስፋ ቃል አስብ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስራኤላውያን ደግመው አንድ ጊዜ ይህን እንዲለምኑኝ አደርጋለሁ፤ ቊጥራቸውንም እንደ በጎች መንጋ አበዛዋለሁ።


ሕልቃናም “ጥሩ ነው፤ መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ፤ ጡት እስክታስጥይውም ድረስ በቤት መቈየት ትችያለሽ፤ እግዚአብሔር የሰጠሽን የተስፋ ቃል ይፈጽምልሽ” ሲል መለሰላት፤ ስለዚህም ሐና በቤት ተቀምጣ ልጇን ታሳድግ ጀመር።