2 ሳሙኤል 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ዳዊት አንዲህ አለ፦ “ኢያቡሳውያንን የሚመታ ዳዊት በሚጠላቸው በዕውሮችና በአንካሶች ላይ አደጋ ለመጣል በውሃው መተላለፊያ ይውጣ፤” ስለዚህም ዕውሮችና አንካሶች ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም ተባለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ዕለት ዳዊት፣ “ኢያቡሳውያንን ድል ማድረግ የሚፈልግ፣ የዳዊት ጠላቶች ወደሚሆኑ፣ ‘ዐንካሶችና ዕውሮች’ ለመድረስ በውሃ መተላለፊያው ሽቅብ መውጣት አለበት” አለ። እንግዲህ፣ “ ‘ዐንካሶችና ዕውሮች’ ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም” ያሉት ለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ዕለት ዳዊት፥ “ኢያቡሳውያንን መግደል የሚፈልግ፥ የዳዊት ጠላቶች ወደሚሆኑ፥ ‘አንካሶችና ዕውሮች’ ለመድረስ በውሃ መተላለፊያው ይውጣ” አለ። ለዚህም ነበር፥ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም” የተባለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ዳዊት፦ ኢያቡሳውያንን የሚመታ በውኃ መሄጃው ይውጣ፥ የዳዊትም ነፍስ የምትጠላቸውን ዕውሮችንና አንካሶችን ያውጣ አለ። ስለዚህም በምሳሌ፦ ዕውርና አንካሳ ወደ ቤት አይግቡ ተባለ። |
ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።
እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸውም እንዲህ ይባባሉ ነበር፤ “ይህ በየቀኑ እስራኤልን ለመፈታተን የሚወጣውን ሰው ታያላችሁን? ንጉሥ ሳኦል እርሱን ለሚገድልለት ሰው ብዙ ሀብት ለመስጠት ቃል ገብቶአል፤ ሴት ልጁንም እንደሚድርለትና የአባቱም ቤተሰብ ከግብር ነጻ እንደሚያደርግለት ተናግሮአል።”