ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤
2 ሳሙኤል 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በነገሠበት ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በጠቅላላ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ አርባ ዓመትም ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ፤ አርባ ዓመትም ገዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ አርባ ዓመትም ነገሠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ዓመት ልጅ ነበረ፥ አርባ ዓመትም ነገሠ። |
ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤
ከኬብሮናውያንም በቤተሰብ የትውልድ ምዝገባ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበር፤ ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት በመዝገቡ ውስጥ ፍለጋ ተደርጎ በገለዓድ ያዕዜር ችሎታ ያላቸው ኬብሮናውያን ተገኙ፤
እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት በኬብሮን ሲሆን ዳዊት መኖሪያውን በዚያ አድርጎ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ወቅት ነው። ዳዊት መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ ሦስት ዓመት ገዛ፤
ኢየሱስ የማስተማር ሥራውን ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያኽል ሆኖት ነበር፤ ለሕዝቡ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር፤ ይኸውም ዮሴፍ የዔሊ ልጅ፥