2 ሳሙኤል 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔር ለብንያም ነገድ ሕዝብም ይህንኑ ተናገረ፤ ከዚያም በኋላ የብንያምና የእስራኤል ሕዝብ ለማድረግ የተስማሙበትን ጉዳይ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም አበኔር ለብንያማውያን ራሱ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አበኔር ሄዶ ይህንኑ ለብንያማውያን ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም ደግሞ በብንያም ልጆች ጆሮ ተናገረ፤ አበኔርም ደግሞ በእስራኤልና በብንያም ቤት ሁሉ መልካም የነበረውን ለዳዊት ሊነግረው ወደ ኬብሮን ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም ደግሞ በብንያም ወገን ጆሮ ተናገረ፥ አበኔርም ደግሞ በእስራኤልና በብንያም ቤት ሁሉ መልካም የነበረውን ለዳዊት ሊነግረው ወደ ኬብሮን ሄደ። |
በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።