2 ሳሙኤል 23:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን ለመዳሰስ የብረት ልብስ ወይም የጦር ዛቢያ ያስፈልጋል፤ በዚያን ጊዜ ባሉበት ፈጽመው ይቃጠላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣ የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሾኽ የሚነካ ሁሉ፥ የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ እነሱም ባሉበት ስፍራ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእሳት ከሚቃጠሉና በውርደታቸው ከሚነድዱ በቀር በብረት ብዛትም ሆነ፥ በጦር ዘንግ ብዛት ሰው የሚደክምባቸው አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ይነካው ዘንድ ቢወደድ፥ በእጁ ብረትና የጦሩን የቦ ይይዛል፥ በሥራቸውም በእሳት ፈጽሞ ይቃጠላሉ። |
“ነገር ግን የሰው ልጅ ሆይ! እነርሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ፤ እንደ እሾኽና እንደ አሜከላ ሆነውብህ በጊንጦች መካከል እንደምትኖር ሆነህ ቢሰማህም ቃላቸውንም ሆነ የእነዚያን ዐመፀኞች የቊጣ ፊት ከቶ አትፍራ።
ስለዚህ ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜ ዐጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳት እንዲቃጠልም በየነዶው እሰሩ፤ ስንዴውን ግን ሰብስቡና በጐተራዬ ክተቱ’ እላቸዋለሁ።”
ከሰማይ የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀጣቸዋል።