ስለዚህም በተቆዓ የምትኖረውን አንዲት ብልኅ ሴት አስጠራ፤ እርስዋም በደረሰች ጊዜ “ሐዘንተኛ ለመምሰል ሞክሪ፤ የሐዘን ልብስሽን ልበሺ፤ ቅቤም አትቀቢ፤ ለብዙ ጊዜ በሐዘን ላይ የቈየሽ ሴት ለመምሰል ተዘጋጂ፤
2 ሳሙኤል 20:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማይቱ ውስጥ የምትኖር አንዲት ብልኅ ሴት በቅጽሩ ላይ ሆና ድምፅዋን ከፍ በማድረግ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብ ወደዚህ ይመጣ ዘንድ ንገሩት፤ እኔ ላነጋግረው እፈልጋለሁ!” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዲት ብልኅ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ከከተማ ትጣራለች፤ “ስሙ! ስሙ! ለኢዮአብ የምነግረው ነገር ስላለ ወደዚህ እንዲመጣ ንገሩት” አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ አንዲት ብልኅ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፥ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብን ላነጋግርህ እንድችል ወደዚህ ና በሉት” አለቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቅጥሩም አንዲት ብልሃተኛ ሴት፥ “ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮአብንም፦ እነግርህ ዘንድ ወደዚህ ቅረብ በሉት” ስትል ጮኸች። ወደ እርስዋም ቀረበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማይቱም አንዲት ብልሃተኛ ሴት፦ ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮአብንም፦ እነግርህ ዘንድ ወደዚህ ቅረብ በሉት ስትል ጮኸች። |
ስለዚህም በተቆዓ የምትኖረውን አንዲት ብልኅ ሴት አስጠራ፤ እርስዋም በደረሰች ጊዜ “ሐዘንተኛ ለመምሰል ሞክሪ፤ የሐዘን ልብስሽን ልበሺ፤ ቅቤም አትቀቢ፤ ለብዙ ጊዜ በሐዘን ላይ የቈየሽ ሴት ለመምሰል ተዘጋጂ፤
ኢዮአብ ወደዚያ በሄደ ጊዜም ሴትዮዋ “ኢዮአብ የምትባለው አንተ ነህን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” አላት። እርስዋም “ጌታዬ፥ እስቲ አድምጠኝ” አለችው፤ እርሱም “እነሆ፥ አዳምጥሻለሁ” አላት።
ይህንንም ዕቅድ በተግባር ለመግለጥ ወደ ከተማይቱ ሕዝብ ሄደች፤ እነርሱም የቢክሪን ልጅ የሺባዕን ራስ ቈርጠው በግንቡ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፤ እርሱም ወታደሮቹ ከተማይቱን ለቀው ይወጡ ዘንድ ምልክት እንዲሆን እምቢልታ ነፋ፤ እነርሱም ወደየቤታቸው ተመለሱ፤ ኢዮዓብም ንጉሡን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ።
ውሳኔውን በሥራ ላይ እንዲያውል የተመደበው አርዮክ የተባለው የንጉሡ የክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ ስለዚህ ዳንኤል ወደ እርሱ ሄደና በዘዴ አነጋገር፦