ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን አሳደዱት፤ ፀሐይ በጠለቀች ጊዜም ከጊያሕ በስተ ምሥራቅ፥ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደረሱ።
2 ሳሙኤል 2:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ነገድ ሰዎች እንደገና ተሰብስበው ወደ አበኔር መጡ፤ በአንድ ኮረብታም ጫፍ ላይ ለጦርነት በመዘጋጀት ተሰለፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የብንያም ሰዎች ወደ አበኔር ተሰብስበው ግንባር በመፍጠር በኰረብታው ጫፍ ላይ ተሰለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የብንያም ሰዎች ተሰብስበው ከአበኔር ጀርባ በመሆን ግንባር ፈጠሩ፤ በኰረብታውም ጫፍ ላይ ተሰለፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአበኔር ኋላ የነበሩ የብንያምም ልጆች ተሰበሰቡ፥ በአንድነትም ሆኑ፤ በአንድ ኮረብታም ራስ ላይ ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች ወደ አበኔር ተሰበሰቡ፥ በአንድነትም ሆኑ፥ በኮረብታም ራስ ላይ ቆሙ። |
ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን አሳደዱት፤ ፀሐይ በጠለቀች ጊዜም ከጊያሕ በስተ ምሥራቅ፥ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደረሱ።
አበኔርም፥ ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ዘለዓለም ስንዋጋ እንኖራለንን? ፍጻሜውስ መራር መሆኑን አትገነዘብምን? ሰዎችህ እኛን ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸው እስከ መቼ ነው?”