2 ሳሙኤል 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም አበኔር “እኔን ማሳደድህን ተው! ለምን እንድገድልህ ትገፋፋኛለህ? አንተንስ ብገድል የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ማየት እችላለሁ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም አበኔር አሣሄልን፣ “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋራ ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገናም አበኔር፥ “እኔን ማሳደድህን ተው! እኔስ ስለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም አሣሄልን፥ “ከምድር ጋር እንዳላጣብቅህ እኔን ከማሳደድ ፈቀቅ በል፤ ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ፊቴን አቅንቼ አይ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? እንደዚህ አይሆንምና ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ተመለስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም አሣሄልን፦ ከምድር ጋር እንዳላጣብቅህ እኔን ከማሳደዱ ፈቀቅ በል፥ ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ፊቴን አቅንቼ አይ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? አለው። |
አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።
ሳኦልም ሜልኮልን “ጠላቴ የሚያመልጥበትን ተንኰል በመሥራት ስለምን እንዲህ አታለልሽኝ?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እኔ ምን ላድርግ፥ ‘ማምለጥ እንድችል ካልረዳሽኝ እገድልሻለሁ’ አለኝ” ስትል መለሰችለት።