2 ሳሙኤል 2:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም በኬብሮን ተቀምጦ በመላው ይሁዳ ላይ ሰባት ዓመት ተኩል ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በኬብሮን ንጉሥ ሆኖ በይሁዳ የገዛው ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በኬብሮን ነግሶ እስራኤልን የገዛው ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በይሁዳ ቤት በኬብሮን የነገሠበት ዘመን ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በይሁዳ ቤት ነግሦ በኬብሮን የተቀመጠበት ዘመን ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበረ። |
እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት በኬብሮን ሲሆን ዳዊት መኖሪያውን በዚያ አድርጎ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ወቅት ነው። ዳዊት መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ሠላሳ ሦስት ዓመት ገዛ፤