ከዚህም በኋላ ኢዮአብ አገልጋዩ የነበረውን አንድ ኢትዮጵያዊ ጠርቶ “ያየኸውን ሁሉ ሄደህ ለንጉሡ ንገር” አለው፤ አገልጋዩም እጅ ነሥቶ ሮጠ።
2 ሳሙኤል 18:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አገልጋዩም “ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ላይ የደረሰ ነገር በጠላቶችህና በአንተ ላይ በዐመፁት ሁሉ ላይ ይድረስ!” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም፣ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶችና ሊጐዱህ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም፥ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶችና ሊጐዱህ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኩሲን፥ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” አለው። ኩሲም፥ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች፥ በክፉም የተነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ብላቴና ይሁኑ” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኵሲን፦ ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን? አለው። ኵሲም፦ የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች፥ በክፉም የተነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ብላቴና ይሁኑ ብሎ መለሰለት። |
ከዚህም በኋላ ኢዮአብ አገልጋዩ የነበረውን አንድ ኢትዮጵያዊ ጠርቶ “ያየኸውን ሁሉ ሄደህ ለንጉሡ ንገር” አለው፤ አገልጋዩም እጅ ነሥቶ ሮጠ።
ንጉሡም “ወጣቱ አቤሴሎም ምንም ጒዳት አልደረሰበትምን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም “ጌታዬ ሆይ፥ የጦር አዛዥህ ኢዮአብ ወደ አንተ በላከኝ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆኖ አየሁ፤ ነገር ግን ምን እንደ ሆነ መናገር አልችልም” ሲል መለሰ።
በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል እጅግ ከመደንገጡና በሐሳብ ከመታወኩ የተነሣ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ፤ ንጉሡም “ብልጣሶር ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ አያስጨንቅህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ሕልሙም ሆነ ትርጒሙ ለአንተ መሆኑ ቀርቶ ለጠላቶችህ ቢሆን በወደድሁ ነበር።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።
የበቀል እርምጃ በመውሰድ ጠላቶችህን እንዳትገድል የጠበቀህ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ እኔ አሁን በሕያው እግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ፤ ጠላቶችህና አንተን ለመጒዳት የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤