ኢዮአብም “አይሆንም፤ ዛሬ አንተ ይዘኸው የምትሄድ ምንም ዐይነት መልካም ወሬ የለም፤ ምናልባት ሌላ ቀን ይህን ልታደርግ ትችላለህ፤ ዛሬ ግን የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ ይህን ባታደርግ ይሻላል” አለው።
2 ሳሙኤል 18:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዮአብ አገልጋዩ የነበረውን አንድ ኢትዮጵያዊ ጠርቶ “ያየኸውን ሁሉ ሄደህ ለንጉሡ ንገር” አለው፤ አገልጋዩም እጅ ነሥቶ ሮጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፣ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው፤ ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፥ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው። ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየኸውንም ሁሉ ለንጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢዮአብ ሰግዶ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ኵሲን፦ ሂድ ያየኸውንም ለንጉሡ ንገር አለው። ኵሲም ለኢዮአብ እጅ ነሥቶ ሮጠ። |
ኢዮአብም “አይሆንም፤ ዛሬ አንተ ይዘኸው የምትሄድ ምንም ዐይነት መልካም ወሬ የለም፤ ምናልባት ሌላ ቀን ይህን ልታደርግ ትችላለህ፤ ዛሬ ግን የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ ይህን ባታደርግ ይሻላል” አለው።
አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።
አሒማዓጽም እንደገና “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ እኔ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ኢዮአብም “እንግዲያውስ ሂድ” አለው፤ ስለዚህም አሒማዓጽ በዮርዳኖስ ሸለቆ በሚያመራው መንገድ ሲሮጥ ሄዶ ወዲያውኑ ኢትዮጵያዊውን ቀደመው።
ቀጥሎም ኢትዮጵያዊው አገልጋይ እዚያ ደረሰና ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! የምሥራች ቃል ይዤልህ መጥቼአለሁ፤ በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡብህን ድል እንድታደርግ ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶሃል!” አለው።