2 ሳሙኤል 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ኢዮአብም “አይሆንም፤ ዛሬ አንተ ይዘኸው የምትሄድ ምንም ዐይነት መልካም ወሬ የለም፤ ምናልባት ሌላ ቀን ይህን ልታደርግ ትችላለህ፤ ዛሬ ግን የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ ይህን ባታደርግ ይሻላል” አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ኢዮአብም፣ “ዛሬ የምሥራቹን ወሬ የምትወስድለት አንተ አይደለህም፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ፣ ዛሬ ሳይሆን፣ የምሥራቹን ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ኢዮአብም፥ “ዛሬ የምሥራቹን ወሬ የምትወስድለት አንተ አይደለህም፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ፥ ዛሬ ሳይሆን የምሥራቹን ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ” አለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ኢዮአብም፥ “አንተ በዚች ቀን የምሥራች የምትናገር ሰው አይደለህም፤ ወሬውን በሌላ ቀን ትናገራለህ፤ በዚች ቀን ግን የንጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አትናገርም” አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ኢዮአብም፦ በሌላ ቀን እንጂ ዛሬ ወሬ አትናገርም፥ የንጉሥ ልጅ ሞቶአልና ዛሬ ወሬ አትናገርም አለው። Ver Capítulo |