2 ሳሙኤል 16:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በሠራዊቱና በክብር ዘበኞቹ መካከል እያለ ሺምዒ በዳዊትና በመኳንንቱ ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡ ወታደሮችና የክብር ዘቦቹ ሁሉ በዳዊት ግራና ቀኝ ቢኖሩም እንኳ፣ በዳዊትና በሹማምቱ ላይ ሁሉ ድንጋይ ይወረውርባቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ቢኖሩም እንኳ፥ ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሥ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ባሪያዎች ድንጋይ ይወረውር ነበር፥ በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኃያላኑ ሁሉ ነበሩ። |
“ንጉሥ ሆይ! ከኢየሩሳሌም ወጥተህ በሄድክበት ቀን ያደረግኹትን በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ ቂም በቀልም አትያዝብኝ፤ ዳግመኛም ስለ እርሱ አታስብ፤