ከዚህ በኋላ ዳዊትና ሠራዊቱ ባመሩበት መንገድ ተጓዙ፤ ሺምዒም በኮረብታው ጥግ እነርሱን ተከትሎ እየሄደ በመራገም ድንጋይና ዐፈር በእነርሱ ላይ ይወረውር ነበር።
2 ሳሙኤል 16:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዕረፍት አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ለመሄድ ወዳሰቡበት ስፍራ ደረሱ፤ በጣም ደክሟቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደረሱ፤ ደክመውም ነበር፤ በዚያም ዐረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደክመው ነበር፥ በዚያም ዐረፉ። |
ከዚህ በኋላ ዳዊትና ሠራዊቱ ባመሩበት መንገድ ተጓዙ፤ ሺምዒም በኮረብታው ጥግ እነርሱን ተከትሎ እየሄደ በመራገም ድንጋይና ዐፈር በእነርሱ ላይ ይወረውር ነበር።
ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤