ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።
2 ሳሙኤል 14:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ አንድ ቀን ገላጋይ በሌለበት ስፍራ ሁለቱ ልጆቼ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ገደለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፣ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ አገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፤ ገላጋይም ስላልነበረ፥ አንዱ ሌላውን መትቶ ገደለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኔም ለአገልጋይህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፤ በሜዳም ተጣሉ፤ የሚገላግላቸውም አልነበረም፤ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእኔም ለባሪያህ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፥ በሜዳም ተጣሉ፥ የሚገላግላቸውም አልነበረም፥ አንዱም ሌላውን መትቶ ገደለው። |
ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።
አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው።
ስለዚህ አገልጋዮቹ አቤሴሎም በነገራቸው መመሪያ መሠረት አምኖንን ገደሉ፤ የቀሩትም የዳዊት ወንዶች ልጆች በበቅሎዎቻቸው ተቀምጠው እየጋለቡ ሸሹ።
ንጉሥ ሆይ! እነሆ አሁን ዘመዶቼ ሁሉ በእኔ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው ‘ወንድሙን ስለ ገደለ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን ሰው ስጪን’ እያሉ አስቸገሩኝ። ታዲያ፥ እንዲህ የሚያደርጉ ከሆነ የቀረኝን አንድ ተስፋ ሊያጠፉብኝና በምድርም ላይ የባሌን ስምና ዘር ሊያሳጡ ነው።”
በማግስቱም ወደዚያው ስፍራ ተመልሶ ሲሄድ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ በደል የሠራውንም ሰው ተመልክቶ “ወገንህ የሆነውን ዕብራዊ ለምን ትመታዋለህ?” ሲል ጠየቀው።