ከዚያን በኋላ ወደ ንጉሡ ቀርቦ እንዲጠይቅለት ኢዮአብን አስጠራ፤ ኢዮአብ ግን መምጣት አልፈቀደም፤ አቤሴሎም እንደገና ኢዮአብ እንዲመጣለት መልእክት ላከ፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ፤
2 ሳሙኤል 14:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም አቤሴሎም አገልጋዮቹን “ተመልከቱ፤ የኢዮአብ እርሻ ከእኔ እርሻ ቀጥሎ ሲሆን የገብስ ሰብል ይገኝበታል፤ ስለዚህም ሂዱና በእሳት አቃጥሉት” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሄደው ሰብሉን በእሳት አቃጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ የኢዮአብ ዕርሻ የሚገኘው ከእኔ ዕርሻ አጠገብ ነው፤ በዕርሻው ላይ የገብስ አዝመራ አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው የኢዮአብን ዕርሻ በእሳት አቃጠሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ፥ የኢዮአብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይ የገብስ ሰብል አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው እርሻውን በእሳት አቃጠሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ብላቴኖቹን፥ “በእርሻዬ አጠገብ ያለችውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፤ በዚያም ገብስ አለው፤ ሄዳችሁ በእሳት አቃጥሉት” አላቸው። የአቤሴሎምም ብላቴኖች እርሻውን አቃጠሉት። የኢዮአብም አሽከሮች ልብሶቻቸውን ቀድደው ተመልሰው፥ “የአቤሴሎም አሽከሮች እርሻህን በእሳት አቃጠሉት” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹንም፦ በእርሻዬ አጠገብ ያለውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፥ በዚያም ገብስ አለው፥ ሂዳችሁ በእሳት አቃጥሉት አላቸው። የአቤሴሎምም ባሪያዎች እርሻውን አቃጠሉት። |
ከዚያን በኋላ ወደ ንጉሡ ቀርቦ እንዲጠይቅለት ኢዮአብን አስጠራ፤ ኢዮአብ ግን መምጣት አልፈቀደም፤ አቤሴሎም እንደገና ኢዮአብ እንዲመጣለት መልእክት ላከ፤ ኢዮአብ ግን አሁንም ሳይመጣ ቀረ፤
ኢዮአብም “እኔ አሁን ከአንተ ጋር ጊዜ ማባከን አልፈልግም” አለውና ሦስት ጦሮችን ወስዶ አቤሴሎም በወርካው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት ሳለ በደረቱ ተከለበት።
ኢዩም “ኤልዛቤልን ወደታች ወርውሩአት!” አላቸው፤ እነርሱም አንሥተው በወረወሩአት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በሬሳዋ ላይ ፈረሶቹንና ሠረገላውን ነዳበት፤