ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።
2 ሳሙኤል 14:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተነሥቶም ወደ ገሹር ሄደ፤ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አመጣው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ወደ ጌሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ ወደ ገሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ ጌድሶር ሄደ፤ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፥ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም ይዞ መጣ። |
ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።
ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው ታልማይ ተብሎ የሚጠራው የገሹር ንጉሥ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥
ከምናሴ ነገድ ወገን የሆነው ያኢር መላውን የአርጎብ ምድር ወረሰ፤ ይህችውም እስከ ገሹርና እስከ ማዕካ ጠረፍ የምትደርሰው ባሳን ናት፤ መንደሮቹንም በእርሱ ስም እንዲጠሩ አደረገ፤ ስለዚህ እነርሱ የያኢር መንደሮች ተብለው እስከ ዛሬ ይጠራሉ።