የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ውብ የሆነች ትዕማር ተብላ የምትጠራ፥ ገና ባል ያላገባች እኅት ነበረችው፤ አምኖን ተብሎ የሚጠራው ከዳዊት ልጆች አንዱ ትዕማርን ወደዳት፤
2 ሳሙኤል 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋንም እጅግ ከማፍቀሩ የተነሣ ታመመ፤ ድንግል ስለ ነበረች እርስዋን መገናኘት ከቶ አልተቻለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምኖን እኅቱን ትዕማርን ከማፍቀሩ የተነሣ እስኪታመም ድረስ ተጨነቀ፤ ድንግል ስለ ሆነች እርሷን ማግኘት የማይቻል ሆኖ አግኝቶታልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቱን ትዕማርን ያፈቀረው አምኖን እስኪታመም ድረስ እጅግ ተሰቃየ፤ ድንግል ነበረችና አንዳች ነገር እንዳያደርግባት የማይታሰብ ሆኖበት አስጨነቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እስከሚታመም ድረስ እጅግ ተከዘ፤ ድንግልም ነበረችና አንዳች ነገር ያደርግባት ዘንድ በዐይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ ታመመ፥ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር። |
የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ውብ የሆነች ትዕማር ተብላ የምትጠራ፥ ገና ባል ያላገባች እኅት ነበረችው፤ አምኖን ተብሎ የሚጠራው ከዳዊት ልጆች አንዱ ትዕማርን ወደዳት፤
አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ሐዘን ወደ መዳን የሚመራ በንስሓ የሚገኘውን ለውጥ ስለሚያስገኝ ጸጸትን አያስከትልም፤ ዓለማዊ ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።