2 ሳሙኤል 11:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ተቈጥቶ እንዲህ ይልህ ይሆናል፥ ‘እነርሱን ለመውጋት ወደ ከተማይቱ ለምን ተጠጋችሁ? በግንብ ላይ ሆነው ፍላጻዎችን እንደሚወረውሩባችሁ አላወቃችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ በቍጣ ቱግ ብሎ ‘ለመዋጋት ስትሉ ይህን ያህል ወደ ከተማዪቱ የተጠጋችሁት ስለ ምንድን ነው? ከግንቡ ቅጥር በላይ ፍላጻ እንደሚሰድዱባችሁ አታውቁም ኖሯል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ በቁጣ ቱግ ብሎ እንዲህ ይልህ ይሆናል፥ ‘ለመውጋት ስትሉ ይህን ያህል ወደ ከተማዪቱ የተጠጋችሁት ስለ ምንድነው? ከግንቡ ቅጥር በላይ ፍላጻ እንደሚሰዱባችሁ አታውቁም ኖሮአል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡ ቢቈጣ፥ እንዲህም ቢል፦ ልትዋጉ ወደ ከተማዪቱ ለምን ቀረባችሁ? ከቅጥሩ በላይ ፍላጻ እንዲወረወር አታውቁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስትዋጉ ወደ ከተማይቱ ለምን ቀረባችሁ? ከቅጥሩ በላይ ፍላጻ እንዲወረወር አታውቁምን? |
የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ እንዴት እንደ ሞተ አታስታውሱምን? እርሱን ቴቤጽ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ አንዲት ሴት ከግንብ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል ገደለችው፤ ታዲያ እናንተ ወደ ግንብ የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ ንጉሡ ይህን ጥያቄ ቢያቀርብልህ፥ ‘የጦር መኰንንህ ኦርዮም ተገድሎአል’ ብለህ ንገረው።”