Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 11:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ እንዴት እንደ ሞተ አታስታውሱምን? እርሱን ቴቤጽ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ አንዲት ሴት ከግንብ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል ገደለችው፤ ታዲያ እናንተ ወደ ግንብ የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ ንጉሡ ይህን ጥያቄ ቢያቀርብልህ፥ ‘የጦር መኰንንህ ኦርዮም ተገድሎአል’ ብለህ ንገረው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤጽ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ አንተም መልሰህ፥ ‘አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኔር ልጅ የይ​ሩ​በ​ዓ​ልን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ እን​ደ​ዚህ ቀረ​ባ​ችሁ? አን​ተም፦ ባሪ​ያህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላ በቴቤስ ላይ የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ስለ ምን ወደ ቅጥሩ እንደዚህ ቀርባችሁ? ብሎ ንጉሡ ሲቆጣ ብታይ፥ አንተ፦ ባሪያህ ኬጢያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 11:21
11 Referencias Cruzadas  

የጠላት ወታደሮች ከከተማይቱ ወጥተው የኢዮአብን ሠራዊት ወጉ፤ ከዳዊት የጦር መኰንኖች ጥቂቶቹ ሞቱ፤ ኦርዮም አብሮ ሞተ።


ንጉሡ ተቈጥቶ እንዲህ ይልህ ይሆናል፥ ‘እነርሱን ለመውጋት ወደ ከተማይቱ ለምን ተጠጋችሁ? በግንብ ላይ ሆነው ፍላጻዎችን እንደሚወረውሩባችሁ አላወቃችሁምን?


ስለዚህም መልእክተኛው ወደ ዳዊት ሄዶ ኢዮአብ ያዘዘውን ሁሉ እንዲህ ሲል ነገረው፤


አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።


እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ አልታበቱም፤ ታዲያ፥ በዚህ ሁኔታ ሳለ በወንጀለኞች እጅ እንደሚወድቅ ሰው እንዴት ተገደልክ!” ሕዝቡም ሁሉ ስለ እርሱ እንደገና አለቀሱ።


ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ ሞኞች እንዲሳለቁብኝ አታድርግ።


እንዲህም ይሉታል፥ ‘አንተም ደግሞ እንደኛ ደካማ ሆንክ! ከእኛም እንደ አንዱ ሆንክ


ከዚህ በኋላ ኢዮአስ “ፈራርሶ የወደቀው የእርሱ መሠዊያ ስለ ሆነ እስቲ ይችል እንደ ሆነ ባዓል ራሱን ይከላከል፤” ለማለት ፈልጎ፥ ለጌዴዎን ይሩባዓል የሚል ስም አወጣለት።


በማግስቱም ማለዳ ይሩባዓል የተባለው ጌዴዎንና ተከታዮቹ በጧት ማልደው ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያን ሰፈርም ከእነርሱ በስተሰሜን በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆ ውስጥ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos