2 ሳሙኤል 11:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ኦርዮን ራት ጋበዘውና እስኪሰክር ድረስ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ አደረገው፤ በዚያም ሌሊት ኦርዮ በቤተ መንግሥቱ ዘበኞች ቤት ብርድ ልብሱን በማንጠፍ ተኝቶ ዐደረ እንጂ ወደ ቤቱ አልሄደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮን በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አሽከሮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮ በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አገልጋዮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ጠራው፤ በፊቱም በላና ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው አገልጋዮች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አልወረደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ጠራው፦ በፊቱም በላና ጠጣ፥ አሰከረውም፥ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው ባሪያዎች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፥ ወደ ቤቱም አልወረደም። |
አቤሴሎም ግን “መልካም ነው! አንተ መምጣት ካልፈቀድህ ወንድሜ አምኖን እንዲመጣ አትፈቅድለትምን?” ሲል ጠየቀ። ንጉሡም “እርሱስ ቢሆን ለምን ይመጣል?” ሲል ጠየቀው።
ሐዘንና ትካዜ የሚደርስበት ማን ነው? ዘወትር ክርክርና ጭቅጭቅ የሚያነሣሣ ማን ነው? ምክንያቱን ሳያውቅ ተፈንክቶ የሚገኝ ማን ነው? ዐይኑ የሚቀላበት ማን ነው?