2 ሳሙኤል 1:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ኀያላን እንዴት ወደቁ? የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀያላኑ እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ከንቱ ይሁኑ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀያላን እንዴት ወደቁ! የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ጠፉ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃዎች እንዴት ጠፉ!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃ እንዴት ጠፋ! |
ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፥ ድምፁን ከፍ በማድረግ “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!” እያለ አለቀሰለት።
ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከሐዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤
እነርሱም በምድር ዳርቻ ከሚገኙ ከሩቅ አገሮች የመጡ ናቸው፤ እግዚአብሔር አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት የቊጣ መሣሪያ የሆነ ሠራዊቱን አሰልፎአል።