ኤልሳዕም “እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! ነገ ይህን ጊዜ በሰማርያ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ሲል መለሰለት።
2 ነገሥት 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም በፍጥነት እየተራወጠ ወጥቶ የሶርያን ሰፈር ዘረፈ፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ በተናገረውም መሠረት ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ተሸመተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሕዝቡ ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አንድ መስፈሪያ ማለፊያ ዱቄት በአንድ ሰቅል፣ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ተሸጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም በፍጥነት እየተራወጠ ወጥቶ የሶርያን ሰፈር ዘረፈ፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ በተናገረውም መሠረት ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ተሸመተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፥ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ተሸመተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል እንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፥ ሁለትም መስፈሪያ ገብስ በአንድ ሰቅል ተሸመተ። |
ኤልሳዕም “እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! ነገ ይህን ጊዜ በሰማርያ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ሲል መለሰለት።
ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።
ከዚህ በኋላ ኢዮሣፍጥና ወታደሮቹ ምርኮ ለመውሰድ ወደዚያ ሄዱ፤ ብዙ የቀንድ ከብት፥ ስንቅና ትጥቅ፥ ልብስና ሌላም ውድ የሆኑ ዕቃዎች አገኙ፤ ምርኮውንም ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀባቸው፤ ነገር ግን ምርኮው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ሁሉንም መውሰድ አልቻሉም፤
አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።
ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ።
የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።