2 ነገሥት 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብረውም ሄዱ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቊረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብሯቸውም ሄደ። ወደ ዮርዳኖስም ሄደው ዛፎች መቍረጥ ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብረውም ሄዱ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቁረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ እንጨት ቈረጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ እንጨት ቆረጡ። |
ከእነርሱም አንዱ ዛፍ በመቊረጥ ላይ ሳለ በድንገት መጥረቢያው ከዛቢያው ላይ ወድቆ ውሃ ውስጥ ገባ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመጮኽ “ጌታዬ ሆይ! እንግዲህ ምን አደርጋለሁ? መጥረቢያው የተውሶ ነው!” ሲል ለኤልሳዕ ነገረው።
ለምሳሌ፥ ሁለት ሰዎች እንጨት ለመቊረጥ ቢሄዱና አንደኛው እንጨቱን ሲቈርጥ የመጥረቢያው ራስ ከዛቢያው ወልቆ በድንገት ሲወረወር ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል፥ ገዳዩ ከእነዚህ ከሦስት ከተማዎች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሕይወቱን ያትርፍ።