እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርስዋ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርስዋም አይሁን! ለሁለት ይቈረጥ!” አለች።
2 ነገሥት 6:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የእኔን ልጅ ቀቅለን በላን፤ በማግስቱም ‘ልጅሽን አምጪና እንብላ’ ብዬ ጠየቅኋት፤ እርስዋ ግን ደበቀችው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ልጄን ቀቅለን በላነው። በማግስቱም፣ ‘እንድንበላው ልጅሽን አምጪው’ አልኋት፤ እርሷ ግን ደበቀችው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የእኔን ልጅ ቀቅለን በላን፤ በማግስቱም ‘ልጅሽን አምጪና እንብላ’ ብዬ ጠየቅኋት፤ እርሷ ግን ደበቀችው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄንም ቀቅለን በላነው፤ በማግሥቱም፦ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው” ብላ መለሰችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጄንም ቀቅለን በላነው፤ በማግሥቱም ‘እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤’ አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው፤” ብላ መለሰችለት። |
እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርስዋ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርስዋም አይሁን! ለሁለት ይቈረጥ!” አለች።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፦ “እናት የምታጠባውን ልጅዋን ልትረሳ ትችላለችን? ወይስ ለወለደችው ልጅ አትራራምን? እርስዋ እንኳ ብትረሳ እኔ ግን እናንተን አልረሳም።
እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን መኖሪያ ከተሞችህን ሁሉ ይከባሉ፤ አንተ የምትተማመንባቸውን ከፍተኞች የሆኑ ቅጽሮች ያሉአቸውን ምሽጎችህን ሁሉ ይደመስሳሉ።
“ጠላቶችህ ከተሞችህን ከበው በሚያስጨንቁህም ጊዜ፥ የምትበላው አጥተህ ግራ ሲገባህ እግዚአብሔር አምላክህ የሰጠህንና የሆድህ ፍሬዎች የሆኑትን ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ሥጋ ለመብላት ትገደዳለህ፤
በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው፥ በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው የጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላ ነገር ስለሌላት በምሥጢር ከምትበላቸው ከማሕፀንዋ ከወጡ ልጆችዋና ከእንግዴልጅዋ ለማንም አትሰጥም።