2 ነገሥት 4:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጅዋን ይዛ ሄደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ገብታ በእግሩ ላይ ወደቀች፤ በምድርም ላይ ተደፋች፤ ልጇንም ይዛ ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጇን ይዛ ሄደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴትዮዋም ገብታ በእግሩ አጠገብ ወደቀች በምድርም ላይ ሰገደች፤ ልጅዋንም አንሥታ ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገብታም በእግሩ አጠገብ ወደቀች፤ በምድርም ላይ ተደፋች፤ ልጅዋንም አንሥታ ወጣች። |
ከኢያሪኮ የመጡት ነቢያት እርሱን ባዩት ጊዜ “በኤልያስ ላይ ዐድሮ የነበረው የመንፈስ ኀይል በኤልሳዕ ላይ አርፏል!” አሉ፤ ወደ እርሱም በመቅረብ ጐንበስ ብለው እጅ ነሡት
ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርስዋ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።
ሴቶች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን ከሞት ተነሥተው አገኘአቸው። ሌሎችም የበለጠ ትንሣኤ ለማግኘት አስበው ልዩ ልዩ ሥቃይ ተቀበሉ፤ ከእስራት ነጻ መሆንንም አልፈቀዱም።