2 ነገሥት 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንገትም “ራሴን! ራሴን!” ብሎ ወደ አባቱ ጮኸ። አባትየውም አንዱን አገልጋይ ጠርቶ፥ “ልጁን ወደ እናቱ ውሰድ” ሲል አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቱንም፣ “ራሴን! ራሴን!” አለው። አባቱም አገልጋዩን፣ “ተሸክመህ ወደ እናቱ አድርሰው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድንገትም “ራሴን! ራሴን!” ብሎ ወደ አባቱ ጮኸ። አባትየውም አንዱን አገልጋይ ጠርቶ፥ “ልጁን ወደ እናቱ ውሰድ” ሲል አዘዘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም ሎሌውን፥ “ተሸክመህ ወደ እናቱ ውስደው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱንም “ራሴን! ራሴን!” አለው፤ እርሱም ሎሌውን “ተሸክመህ ወደ እናቱ ውሰደው፤” አለው። |
ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም።