የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ።
2 ነገሥት 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳም ንጉሥ በኢዮሣፍጥ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመተ መንግሥት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ ዐሥራ ሁለትም ዓመት ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳም ንጉሥ በኢዮሣፍጥ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ነገሠ። |
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ሁለት ዓመት ገዛ።
እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።
ስለዚህም ንጉሥ ኢዮራምና እንዲሁም የይሁዳና የኤዶም ነገሥታት ለዘመቻ ወጡ፤ ከሰባት ቀን ጒዞም በኋላ ውሃ አለቀባቸው፤ ለሠራዊቱም ሆነ ለጭነት እንስሶች ምንም ውሃ አልነበረም።
የእነርሱንም ምክር ተከትሎ በሶርያ ንጉሥ አዛሄል ላይ በተደረገው ጦርነት ከእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ጋር ተባበረ፤ ጦርነቱም በገለዓድ በምትገኘው በራሞት አጠገብ ተደርጎ በዚያ ውጊያ ላይ ኢዮራም ቈሰለ፤