2 ነገሥት 21:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሔፍጺባ ተብላ የምትጠራ ነበረች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናሴ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐምሳ ዐምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐፍሴባ ትባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሔፍጺባ ተብላ የምትጠራ ነበረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናሴም በነገሠ ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ኀምሳ አምስት ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም ሐፍሴባ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናሴም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አምሳ አምስት ዓመት ነገሠ፤ የእናቱ ስም ሐፍሴባ ነበረ። |
ሕዝቅያስ ሞተ፤ በላይኛው ክፍል በሚገኘውም በዳዊት ልጆች መካነ መቃብር ተቀበረ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብም ሁሉ ታላቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት አደረጉለት፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ።
ከእንግዲህ ወዲህ “የተተወች” ተብለሽ አትጠሪም፤ ምድርሽም “ባድማ” ተብላ አትጠራም። የምትጠሪበትም አዲስ ስም፥ “እግዚአብሔር በእርስዋ ደስ ይለዋል!” የሚል ይሆናል፤ ምድርሽም “ባለ ባል” ተብላ ትጠራለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባል እንዳላት ሴት ትሆናለች።
የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን በኢየሩሳሌም ስለ ፈጸመው ክፋት ሁሉ በእነርሱ ላይ ከሚደርሰው ነገር የተነሣ የዓለም ሕዝብ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ።”