2 ነገሥት 17:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ጋራ የገባሁትን ኪዳን አትርሱ፤ ሌሎች አማልክትም አታምልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ሌሎችንም አማልክት አትፍሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ሌሎች አማልክትንም አትፍሩ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እርግጠኞች ሁኑ፤ ምንም ዐይነት የተቀረጸ ምስል እንዳትሠሩ፤ የነገራችሁንም ትእዛዝ ፈጽሙ።
እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና አሁን ምድራቸውን የወረሳችኋቸውን የአሞራውያንን ባዕዳን አማልክት እንዳታመልኩ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አልሰማችሁኝም።”