La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 16:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አካዝም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ ያ መሠዊያ በትክክል መሠራቱን ለማየትና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ ከደማስቆ ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ መሠዊያውን አየ፤ ቀርቦም በመሠዊያው ላይ ወጣ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አካዝም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ ያ መሠዊያ በትክክል መሠራቱን ለማየትና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ከደ​ማ​ስቆ በመጣ ጊዜ መሠ​ዊ​ያ​ውን አየ፤ ንጉ​ሡም ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ከደማስቆ በመጣ ጊዜ መሠዊያውን አየ፤ ንጉሡም ወደ መሠዊያው ቀርቦ በእርሱ ላይ ወጣ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 16:12
8 Referencias Cruzadas  

በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤትኤል ሄደ፤ በዚያም ለእስራኤል በወሰነላቸው መሠረት በዓል ለማክበር በመሠዊያው ላይ መሥዋዕት አቀረበ።


ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተላከ አንድ ነቢይ እነሆ ከይሁዳ መጥቶ እዚያ ደረሰ፤


ስለዚህም ኡሪያ ንጉሥ አካዝ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ልክ ያንኑ የሚመስል መሠዊያ ሠራ፤


እንዲሁም በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፤ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት።


አካዝ ድልን ላጐናጸፉአቸው ለሶርያውያን አማልክት መሥዋዕት አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት “የሶርያ አማልክት የሶርያን ነገሥታት ረድተዋል፤ መሥዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኛል” ብሎ በማሰብ ነው፤ ይህም ድርጊት በራሱና በሀገሩ ላይ ጥፋትን አመጣ፤


በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለባዕዳን አማልክት ዕጣን የሚታጠንባቸውን የኰረብታ የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠራ፤ በዚህም ሁኔታ አካዝ የቀድሞ አባቶቹን አምላክ የእግዚአብሔርን ቊጣ በራሱ ላይ አመጣ።