2 ነገሥት 14:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር “ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እግዚአብሔር፣ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢአቱ ይሙት እንጂ ወላጆች በልጆቻቸው አይገደሉ፣ ልጆችም በወላጆቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ሲል ያዘዘ በመሆኑ፣ የነፍሰ ገዳዩን ልጆች አልገደላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር “ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣ” ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፥ “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች ስለ ልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም ስለ አባቶች አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም በአባቶች አይሙቱ፤” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም። |
ሞት የሚገባው ኃጢአት ለሚሠራ ሰው ብቻ ነው፤ ልጅ ስለ አባቱ ኃጢአት አይቀጣም፤ አባትም ስለ ልጁ ኃጢአት አይቀጣም፤ ደግ ሰው በደግነቱ መልካም ዋጋውን ያገኛል፤ ክፉ ሰውም በክፋቱ ይቀጣል።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
“ልጆቻቸው በሠሩት ወንጀል ወላጆች በሞት መቀጣት የለባቸውም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ወንጀል ልጆቻቸው በሞት አይቀጡ፤ እያንዳንዱ ሰው በሠራው ወንጀል በሞት ይቀጣ።