2 ነገሥት 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰንበት ቀን ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ግን በንጉሡ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ እንደተለመደው በሰንበት ዕለት ከዘብ ጥበቃ ነጻ የምትሆኑት ሁለት ሦስተኛው እጅ ግን ንጉሡ ያለበትን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰንበት ቀን ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ግን በንጉሡ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተም በሰንበት ቀን የምትወጡት ሁለቱ እጅ ንጉሥ ያለበትን የእግዚአብሔርን ቤት ጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም በሰንበት ቀን የምትወጡት ሁለቱ እጅ በንጉሥ ዙሪያ ሆናችሁ የእግዚአብሔርን ቤት ጠብቁ። |
ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል።”
በአገልግሎት ላይ ከሚገኙት ካህናትና ሌዋውያን በቀር ማንም ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት የለበትም፤ ካህናትና ሌዋውያን ግን ለእግዚአብሔር የተለዩ ስለ ሆኑ መግባት ይፈቀድላቸዋል፤ የቀሩት ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመፈጸም ከቤተ መቅደሱ ውጪ ይሁኑ።