La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 11:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዐታልያ ስለ ተገደለች ሰው ሁሉ ተደሰተ፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ተደሰተ፤ ጎቶልያ ቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሰይፍ ተገድላ ስለ ነበር፣ ከተማዪቱ ጸጥ አለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዐታልያ ስለ ተገደለች ሰው ሁሉ ተደሰተ፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ደስ አላ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፀጥ አለች። ጎቶ​ል​ያ​ንም በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ በሰ​ይፍ ገደ​ሉ​አት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች። ጎቶልያንም በንጉሡ ቤት አጠገብ በሰይፍ ገደሉአት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 11:20
5 Referencias Cruzadas  

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል።


እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየችው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ “ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው! ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።


ሕዝቡም ሁሉ በታላቅ ደስታ ተሞሉ፤ ዐታልያም ተገድላ ስለ ነበር ከተማይቱ ሰላም ሰፍኖባት ጸጥ ብላ ነበር።


ለጻድቃን፥ ሁሉ ነገር ሲሳካላቸው በከተማው ውስጥ ደስታ ይሆናል። ክፉዎች ሲጠፉ ደግሞ እልልታ ይሆናል።


ደጋግ ሰዎች ሲሾሙ ሕዝቦች ይደሰታሉ፤ ክፉ ሰዎች ሲሾሙ ግን ሕዝቦች ይጨነቃሉ።