ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
2 ቆሮንቶስ 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ በሌላው ሰው የሥራ ክልል ውስጥ ገብተን አስቀድሞ በተሠራው ሥራ ሳንመካ ከእናንተ ወዲያ ባሉት አገሮች የምሥራቹን ቃል ለማብሠር እንችላለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሌላው ሰው ክልል አስቀድሞ በተሠራ ሥራ ሳንመካ፣ ከእናንተ ወዲያ ባለው አገር ወንጌልን መስበክ እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌላው ክፍል ስለ ተሠራው ነገር መመካት ሳያስፈልገን፥ ከእናንተ አልፎ ባለው አገር ወንጌልን ለማብሰር ያስችለናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብዝተንም እናስተምራችኋለን፤ ያንጊዜም መጠናችን ከሥራችን ጋር ከፍ ከፍ ይላል፤ እኛስ ቀና ባልሆነውና በማይገባው አንመካም። |
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
እኔ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ ለእናንተ መስበኬና እናንተን ከፍ ለማድረግ ራሴን ማዋረዴ ምናልባት እንደ ኃጢአት ተቈጥሮብኝ ይሆን?