2 ዜና መዋዕል 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እኔ ግርማ ያለው ውብ ቤተ መቅደስ ለአንተ ሠርቼአለሁ፤ ይህም ቤተ መቅደስ አንተ ለዘለዓለም የምትኖርበት ስፍራ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ለዘላለም የምትኖርበትን ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቼልሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ለዘለዓለም እንድትኖርበት ታላቅ የሆነ ማደሪያ ቤትን ሠራሁልህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ለዘለዓለም የሚኖርበት ዝግጁና ቅዱስ ቤት ለስሙ ሠራሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን ለዘላለም ትኖርበት ዘንድ ማደሪያ ቤትን ሠራሁልህ፤” አለ። |
ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞንም እንዲህ አለ፤ “አይዞህ በርታ ሥራውንም በቶሎ ጀምር፤ ምንም ነገር አይግታህ፤ እኔ የማገለግለው እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነው፤ ለቤተ መቅደሱ ሥራ ያለህን አገልግሎት እስክትፈጽም ድረስ ከአንተ አይለይም፤ አይተውህም፤ ከቶም አይጥልህም፤
እግዚአብሔርም “ ‘ቤተ መቅደሴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ እርሱ እንደ ልጄ ይሆናል፤ እኔም እንደ አባት እሆነዋለሁ’ ብሎኛል።
በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በዚያ ቆመው ነበር፤ ንጉሥ ሰሎሞንም ወደ እነርሱ ፊቱን መልሶ፥ የእግዚአብሔር በረከት በእነርሱ ላይ እንዲወርድ እንዲህ ሲል ጸለየ፤
ከዚህም ሁሉ ጋር አንተ ራስህ ከባቢሎን ምድር የሰበሰብከውን ወርቅና ብር፥ የእስራኤል ሕዝብና ካህናታቸውም ጭምር በኢየሩሳሌም በተሠራው የአምላካቸው ቤተ መቅደስ እንዲቀርብላቸው የሚፈልጉትን መባ ሁሉ ይዘህ ሂድ።
እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤