2 ዜና መዋዕል 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቹ ሁሉ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ሌዋውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው፥ ወደ ቤተ መቅደሱ አመጡት፤ እንዲሁም ካህናቱና ሌዋውያኑ እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና በውስጡ የነበሩትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በመጡ ጊዜ ሌዋውያኑ ታቦቱን አነሡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፥ ሌዋውያንም ታቦቱን አነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋውያንም ሁሉ ታቦቷን አነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋውያንም ታቦቱን አነሡ። |
ከዚህም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር ለዘለዓለም እርሱን እንዲያገለግሉና የቃል ኪዳኑንም ታቦት እንዲሸከሙ የመረጣቸው እነርሱን ስለ ሆነ “የቃል ኪዳኑን ታቦት መሸከም የሚገባቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው” አለ።
ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤተ መቅደሱ አግብተው በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከኪሩቤል ክንፎች በታች በሚገኘው ስፍራ አኖሩት።
ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።