2 ዜና መዋዕል 3:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተ መቅደሱን ግድግዳዎች፥ የጣራውን ክፈፎች፥ መቃኖችና መዝጊያዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስሎች ቀረጸባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጣራውን ተሸካሚዎች፣ መቃኖችን፣ የቤተ መቅደሱን ግድግዳና መዝጊያዎች በወርቅ ለበጠ፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቤልን ምስል ቀረጸ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቱንም ሰረገሎቹንም መድረኮቹንም ግንቦቹንም ደጆቹንም በወርቅ ለበጠ በግንቦቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረጸ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቱንም፥ ሰረገሎቹንም፥ መድረኮቹንም፥ ግንቦቹንም፥ ደጆቹንም በወርቅ ለበጠ፤ በግንቦቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረጸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቱንም፥ ሠረገሎቹንም፥ መድረኮቹንም፥ ግንቦቹንም፥ ደጆቹንም በወርቅ ለበጠ፤ በግንቦቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረጸ። |
“እንዲሁም የተቀደሰውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች አብጀው፤ በእነርሱም ላይ ኪሩቤል በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ።