2 ዜና መዋዕል 26:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (ዖዝያ ኤላትን መልሶ በመያዝ ከተማይቱን እንደገና የሠራው ከአባቱ ከአሜስያስ ሞት በኋላ ነው።) አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ አሜስያስ እንደ አባቶቹ ሁሉ ካንቀላፋ በኋላ፣ ኤላትን እንደ ገና የሠራት፣ ወደ ይሁዳም የመለሳት ዖዝያን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ከአንቀላፋ በኋላ ዖዝያን ኤላትን ሠራ፥ ወደ ይሁዳም መለሳት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥ አባቱም ከአባቶቹ ጋር ከአንቀላፋ በኋላ ዖዝያን ኤላትን ሠራ፤ ወደ ይሁዳም መለሳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ከአንቀላፋ በኋላ ዖዝያን ኤላትን ሠራ፤ ወደ ይሁዳም መለሳት። |
በዚያኑ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረጺን የኤላትን ከተማ አስመልሶ በቊጥጥሩ ሥር በማድረግ በዚያ የነበሩትን አይሁድ አስወጣ፤ ያን ጊዜ በኤላት የሰፈሩት ኤዶማውያን እስከ አሁን በዚያ ይገኛሉ።
ንጉሥ ዮአስም አሜስያስን ማርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፤ ከኤፍሬም ቅጽር በር አንሥቶ እስከ ማእዘን ቅጽር በር ድረስ ያለውን ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር ያኽል የሆነውን የኢየሩሳሌምን ቅጽር አፈረሰ።
ዖዝያ በዐሥራ ስድስት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ይኮልያ ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።